Online Library TheLib.net » ከኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም አንደበት: በኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡ ሴራዎች እና ኢትዮጵያውያን የፈፀሙት ታላቅ ስህተት (From Col. Mengistu Haile Mariam's Mouth: Conspiracies Against Ethiopia and the Great Mistake Made by Ethiopians)
cover of the book ከኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም አንደበት: በኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡ ሴራዎች እና ኢትዮጵያውያን የፈፀሙት ታላቅ ስህተት (From Col. Mengistu Haile Mariam's Mouth: Conspiracies Against Ethiopia and the Great Mistake Made by Ethiopians)

Ebook: ከኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም አንደበት: በኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡ ሴራዎች እና ኢትዮጵያውያን የፈፀሙት ታላቅ ስህተት (From Col. Mengistu Haile Mariam's Mouth: Conspiracies Against Ethiopia and the Great Mistake Made by Ethiopians)

00
02.03.2024
0
0
መታሠቢያነቱ፦ ከህግ አግባብ ውጪ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ይሁን።

ከአዘጋጆቹ

በአገራችን ገዥዎች በሰላም ከስልጣን ወርደው ስልጣናቸውን ለሌላው ያስረከቡበት ጊዜ እምብዛም ታይቶ አይታወቅም። ከዚህ ይልቅ የሞት ሽረታቸውን ታግለው ያሸንፋሉ፣ ወይንም ይሸነፋሉ። መጨረሻቸውም ጦር ሜዳ አሊያም ሌላ ቦታ በተደረጉ ሴራና ጦርነቶች ይሆናል።

ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም ልከ እንደ ቀደሙት ገዥዎች ስልጣን ወይንም ሞት ብለው «አንድ ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር ድረስ እንዋጋለን» ብለው የነበር ቢሆንም እሳቸው «ሴራ» በሚሉት በህይወት ከሀገር ወጥተዋል፡፡ ምናልባትም በህይወት በ መኖራቸው በተለያዩ መንገዶች በፖለቲካው ላይ የራሳቸውን አመለካከት ለህዝብ አድርሰዋል።

ኮ/ል መንግስቱ ከሀገር ከወጡ በኋላ እሳቸውን መሰረት አድርገው ጽሁፎች ተጽፈዋል፡፡ በቅርቡ እሳቸውም የራሳቸውን ዳጎስ ያለ መጽሐፍ አሳትመዋል። ይህኛውን የኮ/ል መንግስቱ መልዕከት ልዩ የሚያደርገው ከሀገር አንደወጡ የሰጡትና ምናልባትም አብዛኛውን ስሜታቸውን ሳይደብቁ ያስተላለፉት ኑዛዜ በመሆኑ ነው፡፡ በአገራችን ባህል ኑዛዜ የማይዋሽበት፣ አንድ ሰው በሀይወት እያለ ለቅርብ ቤተሰቦቹም ሊደብቀው የሚቸለውን ሚስጢር ሳይቀር ይፋ የሚያወጣበት ነው፡፡ በዚህ ኑዛዜም ኮ/ል መንግስቱ ከጎናቸው የነበሩት ጓዶቻቸውን «ገመና» በግልጽ ይናገራሉ፡፡ በአንድ ወቅት ትከከለኛ ናቸው ብለው ያምኑባቸው የነበሩትን ነገሮች ስሀተት መሆናቸውን ወይንም መታለላቸውን ያምናሉ። ጄኔራሎች፣ በአገራችን አንቱ የተባሉ እንደ ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያምና ዶ/ር ኃይሉ አርዓያን በወቅቱ ከተቃናቃኝ ቡድኖችና ከውጭ አካላት ጋር ግንኙነት አድርገው እንዳሴሩ አሊያም እንደከዷቸው በኑዛዜያቸው ገልፀውታል።

ከምንም በላይ እርሳቸው ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ባልደረቦቻቸው፣ ተታዋሚዎቻቸውና የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ፈፀሙት የሚሉትን ታላቅ ሴራ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ፈጽመውታል የሚሉትን ሰህተት በኑዛዜ መልከ አስቀምጠውታል። ማን ያውራ የነበረ እንዲሱ ከአንድ የአገር መሪ በኑዛዜ የሚቀርብ መረጃ በቀላሉ የሚታይ አይደለምና በደርግ ዘመን ተፈጠሩ ከሚባሉት ጉዳዮች ውስጥ ለተመራማሪዎች፣ ለታሪከ ፀሐፊዎችና ለቀጣዩ ትውልድም ትልቅ መረጃ ሆኖ ስላገኘነው በመፅሃፍ መልከ አዘጋጅተን አቅርበነዋል።

ምንም እንኳ ከዚህ በኋላ ተረጋግተው የተለያዩ መረጃዎችን ቢሰጡም ይህኛው ኑዛዜያቸው ከሌሎቹ የተሻለ በወቅቱ በተፈጠረባቸው ስሜት እውነታውን ሳይደብቁ ያወጡበት ነው ብለን እናምናለን። ምናልባትም ከዛ በኋላ በሌሎች ደራሲያንና ራሳቸው በጻፉት ላይ ያሉ መረጃዎችን ለማጣቀስም ይህ ኑዛዜያቸው ቀላል የማይባል ትርጉም አንደሚኖረው እምነታችን ነው። መረጃው የተገኘው ኮ/ል መንግስቱ ከአገር እንደወጡ መልዕከታቸውን (ኑዛዜያቸውን) በካሴት ቀርጸው ካስቀመጡት በቀጥታ በመገልበጥ መሆኑንም መግለጽ እንፈልጋለን። መረጃው በካሴት ብልሽት ምከንያት አልያም በውል ከማይሰሙ ድምጾች የተነሳ ከተቀነሱ ጥቂት ገለጻዎች በስተቀር ሙሉ ለሙሉ እንደወረደ የቀረበ ነው። በስተመጨረሻም አዘጋጆቹ ጉዳዩ በመፅሐፍ መልከ ቢቀርብ ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ እንጂ ኮ/ል መንግስቱ የሚያነሱዋቸውን ጉዳዮች በመደገፍም ሆነ፣ የሚነቅፏቸው አካላት ወይንም ሀሳቦች ላይ ተመሳሳይ አቋም በመያዝ እንዳልሆነ አንባቢያን እንዲረዱት ማሳሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ ለተመራማሪዎች፣ ለታሪከ ፀሐፊዎችና ለሰፊው አንባቢ ህዝብ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል ከሚል ብቻ የመነጨ መሆኑን ሳንገልፅ አናልፍም።

መልካም ንባብ
Download the book ከኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም አንደበት: በኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡ ሴራዎች እና ኢትዮጵያውያን የፈፀሙት ታላቅ ስህተት (From Col. Mengistu Haile Mariam's Mouth: Conspiracies Against Ethiopia and the Great Mistake Made by Ethiopians) for free or read online
Read Download
Continue reading on any device:
QR code
Last viewed books
Related books
Comments (0)
reload, if the code cannot be seen