Online Library TheLib.net » የሌ/ኮ መንግሥቱ ያልተነገሩ ምሥጢሮች (The Untold Secrets of Lt. Col. Mengistu Haile Mariam)
cover of the book የሌ/ኮ መንግሥቱ ያልተነገሩ ምሥጢሮች (The Untold Secrets of Lt. Col. Mengistu Haile Mariam)

Ebook: የሌ/ኮ መንግሥቱ ያልተነገሩ ምሥጢሮች (The Untold Secrets of Lt. Col. Mengistu Haile Mariam)

00
02.03.2024
0
0
"መጽሐፍን የሚወድ ሰው መጽሐፍን ማወቅ አለበት" "መጽሐፍ ፀሐፊውን ወይም ደራሲውን ያሳስበዋል"… የሚሉ አባባሎች አሉ። ታድያ እኔ ከነዚህ ሁሉ ደስ የሚለኝ አንድ አባባል አለ "ደራሲያን የአዕምሮና የመንፈስ መሐንዲሶች ናቸው" ይባሳል፤ ልክ ነው። እነሱ ታንፀው ያንጹታል። ይህ አባባል የሊቆቹ አባባል የጎልማሳው አባባል ደግሞ

“በራስህ ዕደግ፣
የጥበብ ፍቅር፤
በውስጥህ ይብራ" የሚል ነው።

ለምን ብትሉኝ ከደራሲያን ብዙ ጥሩ ነገሮችን አግኝቻለሁና ነው፡፡እናም ይህ መጽሐፍ 'ሕይወት በመንግሥቱ ቤተ- መንግሥት" ከተሰኘው መጽሐፍ በይዘቱም ሆነ በቅርጹ ሁሉ የተለየ ሲሆን "ሕይወት በመንግሥቱ ቤተ-መንግሥት" የስቃዩን ዘመንና የጨካኝ ወታደሮችን የግፍ ስራና የግፊኞቹን አፈጻጸም(አገዳደል) ያሳየ ነበር።

የሕይወት በመንግሥቱ ቤተ-መንግሥት ደራሲ እውነተኛነት የሚያሳየው ደራሲው ስማቸው በፎቶግራፍ ተደግፎ ወጥተዋል። እንደ ሌሎቹ ደራሲያን በብፅር ስማቸው ሠርተው በ3ላ ላይ ግን በዋናው ስማቸው አንደሚቀይሩት ደራሲያን ሳይሆኑ ብዙ መኮንኖች እየሰሩ የነበሩትን ሁሉ ያለ ምንም ፍራቻ በድፍረት ነው የጻፉት።

ይህ "የሌ/ኮ መንግሥቱ ያልተነገሩ ምሥጢሮች" መጽሐፍ በአስራ አንድ ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የሌ/ኮ መንግሥቱን የግል ባህሪያቸውንና ሥጋታቸውን አካቶ የተጻፈና ሳይንዛዛ በአጭሩ እውነታዎችን ብቻ ይዞ እየወጣ ነው። ይህን መጽሐፍ ለማዘጋጀት የወጣው ወጪና ድካም ከባድ ቢሆንም በቆራጥነት ወስኖ መስራቱ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን ለአንባቢያን አዲስ አይደለም።

እናም መፅሐፉ ከትውልድ ዘመናቸው ለመነሻነት በመግለጫነት የተነሳውን ነገር ለመነሻ የተወሰደ ሲሆን ያልተነገሩትን ጎላ ጎላ ያሉ እውነታዎች የያዘ ነው። እኔ የተደበቁ ያልተነገሩ ነገሮች ላይ እያነጣጠርኩ ሰራሁ እንጂ የበቃሁ የታሪክ ፀሐፊ አይደለሁም፡ ነገር ግን ለታሪክ ጸሐፊዎችና ሌሎች ባለሙያዎች በመነሻነት ሊያገለግል ይችላል ብዩ አስባለሁ፡፡

ይህ መጽሐፍ በዘመኑ የተፈፀመወን ነገር ያላየው ሁሉ እንዲያውቀው በግልፅ የተፃፈ ነው፡፡ የመፅሐፉ የፊት ለፊት ሽፋን ሌኮ መንግሥቱ ኃማርያም” የሌ/ኮ ማዕረጋቸውን ባገኙበት ጊዜ በደስታ ውስጥ ሆነው የተነሱት ፎቶግራፍ እንደሆነ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ፡፡

"ሕይወት በመንግሥቱ ቤተ-መንግሥት "በተጻፈበት ዘመን ውስጥ ብዙ ሰዎች ሲወዱት አንዳንድ ግለሰቦች ግን እንደሚከፉበትና ለማመን እንደሚቸግራቸው በደንብ አድርጌ አውቀዋለሁ፡፡ እናም እኔን አይደንቀኝም፡፡ ለምን ብትሉኝ እነዚህ ሰዎች በሌኮ መንግሥቱ ዘመነ መንግሥት በስራቸው ላይ ማንነታቸው ይታወቃልና ነው፡፡ ታዲያ እንደነዚህ አይነቶቹን ሰዎች አንድ አባባል በደንብ ይገልፃቸዋል፡፡ 'ድንጋይ ባህር ውስጥ አርባ አመት ይኖራል፤ ግን መዋኘት አይችልም”
Download the book የሌ/ኮ መንግሥቱ ያልተነገሩ ምሥጢሮች (The Untold Secrets of Lt. Col. Mengistu Haile Mariam) for free or read online
Read Download
Continue reading on any device:
QR code
Last viewed books
Related books
Comments (0)
reload, if the code cannot be seen