Online Library TheLib.net » ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ, ቅጽ.2 (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle, Volume 2)
cover of the book ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ, ቅጽ.2 (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle, Volume 2)

Ebook: ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ, ቅጽ.2 (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle, Volume 2)

00
02.03.2024
0
0
ጀነራል ተፈሪ የደርጉ ሊቀመንበር እኔ ነኝ ብለው ሲገልጹ ሌላው የበታች ሹም ተነስቶ ከቡር ጀነራል የደርጉ መሪ ሻለቃ መንግሥቱ እንጅ እርስዎ ያለመሆንዎዖ የአደባባይ ምስጢር ነውና ከእኔ በፊት የተናገረው ጓድ እንዳለው እኔም በከንቱ ወርቃማ ጊዜዎን አያባከኑ የሚል ሃሳብ አቀርባለሁ ሲል ሌሎቹም እንደዚሁ እየተነሱ ብዙ ሕገወጥ የብልግና ነገር ተናገሯቸው። ሁኔታው ሊቀመንበር ተፈሪን የሚያሳፍርና የሚያዋርድ ቢሆንም በታወቀ ትዕግስታቸው የበታች ሹማምንቱን ሃሳብ ለማስለወጥ ብዙ ሙከራ ካደረጉ በኋላ ለዛሬ እዚህ ላይ እናቁምና እናንተም ወደየሰፈራችሁ ሄዳችሁ እንደገና መክራችሁ የሚያስማማንን መፍትሔ ይዛችሁ እንደምትመለሱና ዳግም እዚሁ አንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ በማለት ካሰናበቷቸው በኋላ ስልከ ደውለው የደረሰባቸውን ውርደት ካስረዱኝ በኋላ ሰዎቹ እኔ የምለውን ሊያዳምጡና ሊቀበሉ ቀርቶ ከኔ ጋር ለመነጋገርም ፍላጎት የላቸውምና ምን ባደርግ ይበጃል ትላለሀ፣ ብለው ጠየቁኝ።

ብጀነራል ተፈሪ በንቲን የደርጉ ሲቀመንበር ማድረግና ብጀነራል ጌታቸው ናደውን በቅድሚያ፣ የምድር ጦር አዛዥ በኋላም የኤርትራ ከፍለ ሃገር አስተዳዳሪና የመላው የሰሜን መለዮ ለባሽ ሠራዊት አዛዥ በማድረግ ረገድ የተሰራው ታላቅ ስሀተትየማንም ሳይሆን የእኔ ነበር።

እነ ኡስማን ሳላሕስቤ፣ እነ ረመዳን መሐመድ ኑርና እነ ተማሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ከጀብሐ አፈንግጠው ራሱን ሻቢያ ብሎ የሚጠራውን የጀብሐ አንጃ ድርጅት ከአቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ ገንጣይ ድርጅቶች በሥልጣን ሽሚያ ሲዋጉ ኖረው በዚህ ጊዜ ውስጥ ማለትም በ1969-1970 ዓመታቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር በብዙ የውጊያ ግንባሮች በተወጠረበትና ተዋጊ የሰው ኃይል አጥረት በደረሰበት ጊዜ ከሱማሌ መንግሥት ጋር ተባብረው የኢትዮጵያን አብዮታዊ መንግሥት በመጣል ኤርትራን ይገነጥሉ ዘንድ ያስታረቋቸውና ያስተባበሯቸው በሰላም ፍለጋና በአርቅ ሰበብ ጀነራል አማን መርጠው የላኳቸው ናቸው።

ሞያውና ብቃቱ አላቸው ተብሎ ከተሰባሰቡት መኩንኖች አኔም አንዱ ከመሆኔ ሌላ ከብርጌዱ መምሪያ መከ፡ንኖችም አንዱ በመሆኔ በገነት ጦር ትምህርት ቤት ሻምበል ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በኩሉኔልነት ማዕረግ የሜካናይዝዱ ብርጌድ አዛዥ በሆኑ ጊዜ በሻምበልነት ማዕረግ የቅርብ ረዳታቸው በመሆን አውቃቸዋለሁ። አለባበስ የሚያውቁ፣ ቁንንና ኩሩ፣ በጣም አጭር የማይባል አማካኝ ቁመት፣ ከላይ አስከ ታች የተደላደለና የተገነባ ሰውነት፣ ገብስማ ፀጉርና ግርማ ሞገስ ያላቸው መኩንን ናቸው። ጠቅላላ ባህሪያቸውንና ወታደራዊ አመራራቸውን ስወድ፣ የማልወድላቸው ነገር ቢኖር ጀብደኝነታቸውንና ጉረኝነታቸውን ብቻ ነበርኒ።

507 ግብረ ኃይል ከሞላ ጎደል ሁለት ክፍለ ጦር ሲሆን የግብረ ኃይሉ አዛዥ ኮሎኔል ካሳ ገብረማሪያም፣ የአንደኛው ክፍለ ጦር አዛዥ ሌኮሎኔል አይተነው በላይ ሲሆን የሁለተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ሰይፉ ወልዴ ነበሩ፡፡ ጦሩም ሆነ መሪዎቹ ለወሬ ነጋሪ እንኳን አልተረፉም።
Download the book ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ, ቅጽ.2 (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle, Volume 2) for free or read online
Read Download
Continue reading on any device:
QR code
Last viewed books
Related books
Comments (0)
reload, if the code cannot be seen