Online Library TheLib.net » ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle)
cover of the book ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle)

Ebook: ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle)

00
13.02.2024
0
0
“የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ከተቀጣጠለበት እስከ ተቀለበሰበት ድረስ ያለው ጊዜ ከመሰል ሕዝባዊ አብዮቶች ጋር ስናነፃፅረው በለጋና በአጭር የተቀጨ አብዮት ቢሆንም በአሥራ ሰባት ዓመታት ውስጥ ያደረገውን ፈጣን ጉዞ፣ ያስተናገዳቸውን ሕዝባዊ ተግባሮች፣ የገጠሙትን ፈተናዎችና የጠየቁትን መስዋዕትነት በሦስት ተከታታይ ቅፆች ለማቅረብ ተገድጃለሁ። የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ መሪ ግለሰቦች የሚመጡና የሚሄዱ አላፊዎች ሲሆኑ ሃገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ናቸው። ይህም ቢሆን በአንድ ታሪካዊ ወቅት መንግሥታት፣ የፖለቲካ ደርጅቶች ወይም ግለሰቦች ያከናወኗቸው ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተግባሮች ማንም ወደደ ጠላ የዚያ ሃገርና ሕዝብ ታሪክ ናቸው። ትግላችን ስሙ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በሙሉ ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ በመነሳት ገበሬው ከገባርነት፣ የሠራተኛውን መደብ ከምንዳ ባርነት፣ ጠቅላላውን ባተሌ ሠርቶአደር ሕዝብ ከድንቁርና አረንቋና እጅግ አሳፋሪ ከሆነ የዘላለም ድህነት መንጥቆ በማውጣት ራሱንና አገሩን ለመለወጥ በጀመረው ትግል መሪር መስዋዕትነትን ከፍሎ የትግሉን ጣፋጭ ፍሬ ሳይቀምስ፣ አንድነቱንና ሰላሙን ሳያገኝ እንደገና የጨለመበት አሳዛኝ ሕዝብ ልሳን እንጂ አንባቢን በደስታ ለመመሰጥ የተዘጋጀ የሥነፅሁፍ ድግስ አይደለም። በአብዮት የትግል ጎራ ወይም አሰላለፍ ላይ ብቻ በማተኮር፣ በብቀላ፣ የአጥቂነት ወይም የተከላካይነት ስሜት አጥቅቶኝ በማጋነን ወይም በማቃለል ታሪኩን ላለማዛባት በተቻለኝ መጠን ከራሴ ጋር ታግያለሁ፣ ከህሊናዬም ጋር ተሟግቻለሁ። ይኸ ትግላችን የተሰኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ታሪክ ትምህርት በመስጠቱ ረገድ ስለሚኖረው ፋይዳ ፍርዱን ለአንባቢው እተዋለሁ።” ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሬዝዳንት


“የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ከተቀጣጠለበት እስከ ተቀለበሰበት ድረስ ያለው ጊዜ ከመሰል ሕዝባዊ አብዮቶች ጋር ስናነፃፅረው በለጋና በአጭር የተቀጨ አብዮት ቢሆንም በአሥራ ሰባት ዓመታት ውስጥ ያደረገውን ፈጣን ጉዞ፣ ያስተናገዳቸውን ሕዝባዊ ተግባሮች፣ የገጠሙትን ፈተናዎችና የጠየቁትን መስዋዕትነት በሦስት ተከታታይ ቅፆች ለማቅረብ ተገድጃለሁ።

የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ መሪ ግለሰቦች የሚመጡና የሚሄዱ አላፊዎች ሲሆኑ ሃገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ናቸው። ይህም ቢሆን በአንድ ታሪካዊ ወቅት መንግሥታት፣ የፖለቲካ ደርጅቶች ወይም ግለሰቦች ያከናወኗቸው ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተግባሮች ማንም ወደደ ጠላ የዚያ ሃገርና ሕዝብ ታሪክ ናቸው።

ትግላችን ስሙ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በሙሉ ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ በመነሳት ገበሬው ከገባርነት፣ የሠራተኛውን መደብ ከምንዳ ባርነት፣ ጠቅላላውን ባተሌ ሠርቶአደር ሕዝብ ከድንቁርና አረንቋና እጅግ አሳፋሪ ከሆነ የዘላለም ድህነት መንጥቆ በማውጣት ራሱንና አገሩን ለመለወጥ በጀመረው ትግል መሪር መስዋዕትነትን ከፍሎ የትግሉን ጣፋጭ ፍሬ ሳይቀምስ፣ አንድነቱንና ሰላሙን ሳያገኝ እንደገና የጨለመበት አሳዛኝ ሕዝብ ልሳን እንጂ አንባቢን በደስታ ለመመሰጥ የተዘጋጀ የሥነፅሁፍ ድግስ አይደለም።

በአብዮት የትግል ጎራ ወይም አሰላለፍ ላይ ብቻ በማተኮር፣ በብቀላ፣ የአጥቂነት ወይም የተከላካይነት ስሜት አጥቅቶኝ በማጋነን ወይም በማቃለል ታሪኩን ላለማዛባት በተቻለኝ መጠን ከራሴ ጋር ታግያለሁ፣ ከህሊናዬም ጋር ተሟግቻለሁ።

ይኸ ትግላችን የተሰኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ታሪክ ትምህርት በመስጠቱ ረገድ ስለሚኖረው ፋይዳ ፍርዱን ለአንባቢው እተዋለሁ።”

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም

የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሬዝዳንት

Download the book ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle) for free or read online
Read Download
Continue reading on any device:
QR code
Last viewed books
Related books
Comments (0)
reload, if the code cannot be seen